የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የሁለት ወራት የስራ አፈፃፀም
የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የሁለት ወራት የስራ አፈፃፀም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የሁለት ወራት የስራ አፈፃፀሙን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ። ጳጉሜ 03/2017 ዓ ም የቢሮው የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የማዕከል አመራሮችና የፈፃሚዎች በጋራ ባካሄዱት መድረክ የዘርፉን የሁለት ወራት አፈፃፀም ገምግመዋል። በግምገማ መድረኩ የዘርፉ የሁለት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል። በመድረኩ ከድጋፍ አንፃር ለኢንተርፕራይዞች የተደረገ የብድር፣ የመሳሪያ ሊዝ፣ የአገር ውስጥ ገበያ ትስስር ድጋፍ አበረታች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር እየተሰራ ያለው ስራም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል። በመድረኩ በአምስቱ የእድገት ዘርፎች ለኢንተርፕራይዞች የተደረጉ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሊጋኒ በሰጡት ሀሳብ ለኢንተርፕራይዞች የሚደረጉ ድጋፎች ኢንተርፕራይዞቹን በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲዘልቁ የሚያስችል መሆኑን እያረጋገጥን መሄድ ይገባል ብለዋል። አቶ መሀመድ አያይዘውም ለኢንተርፕራይዞች የሚደረጉ ድጋፎችና የቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች ኢንተርፕራይዞቹን ባሳተፈና እና ገቢያው በሚፈልገው መልኩ በጥናት ላይ በመመስረት የሚከናወን ይሆናል ብለዋል።
No comments yet. Be the first to comment!