የስራ ዕድል ፈጠራ
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ከ67ሺ በላይ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
ስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና
Ephrem Ayalew
September 8, 2025
1228 views
ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በተያዘው የ2018በጀት ዓመት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 67ሺ856 የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል።
ቢሮው የበጀት ዓመቱን የሁለት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ከዘርፉ የክፍለ ከተሞች መዋቅር አመራሮች ጋር በጋራ ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሁለት ወራት በስራ ፈላጊነት ከመዘገባቸው 81ሺ986 ዜጎች ውስጥ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከታቀደው 60ሺ የስራ ዕድል ከዕቅድ በላይ መፈፀም መቻሉ ተገልጿል።
ከተፈጠረው የሥራ ዕድል ውስጥ 43.5 በመቶ የሚሆነው በመደራጀት የተፈጠረ ሲሆን 56.5 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በቅጥር መሆኑን ተመላክቷል።
የስራ ዕድል ፈጠራ እና የስልጠና ተግባራችን ፀጋን መሰረት ያደረገ መሆን ይገባዋል ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ቁጥራዊ መረጃዎችን ከመቀበል ባለፈ ስራዎችን በጥልቀት መፈተሽ ይገባል ብለዋል።
አመራሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባሩን በጥልቀት በመገምገምና በዕውቀት በመምራት ባልተሳኩ ጉዳዮች ላይ በየደረጃው ከሚገኙ ፈፃሚዎች ጋር መግባባት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።
በተለይም ከስልጠና እና ከኢንተርፕራይዞች ማደራጀትና ድጋፍ ጋር በተያያዘ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ክቡር አቶ ጥራቱ አክለውም የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ከፍተኛ የስራ አጥ ምጣኔ ያለባቸውን የከተማዋ አካባቢዎች የርብርብ ማዕከል በማድረግ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ በአጽንዖት ገልጸዋል።
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
No comments yet. Be the first to comment!