የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የጀመረውን የአገልግሎት አሰጣጥና ስታንዴርዳይዜሽን ማኑዋል ትግበራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የተዋቀረ የክትትል ቡድን የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዳይዜሽን ማኑዋል ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ቢሮው ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ የዳሰሳ ተግባር አከናውኗል።

ወርቃማ ሰኞ
August 27, 2025
299 views
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የጀመረውን የአገልግሎት አሰጣጥና ስታንዴርዳይዜሽን ማኑዋል ትግበራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።

ነሀሴ 20፣ 2017 ዓ ም

በአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የተዋቀረ የክትትል ቡድን የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዳይዜሽን ማኑዋል ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ቢሮው ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ የዳሰሳ ተግባር አከናውኗል።

የክትትል ቡድኑን ተቀብለው መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ዮሀንስ የክትትል ስራው  በዝግጅት ምዕራፍ ላይ መደረጉ የተግባር ምዕራፍ ላይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ አጋዥ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

የክትትል ቡድኑ ሰነዶችን በመመልከትና በስራ ክፍሎች በአካል በመገኘት ባካሄደው ቅኝት ቢሮው የአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ማኑዋልን ተግባራዊ ለማድረግ የጀመራቸው ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጿል።

የክትትል ቡድኑ በሰጠው የማጠቃለያ አስተያየት ቢሮው የተቋም ዕቅድን እስከ ግለሰብ ከማውረድ ጀምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ቀልጣፋና ወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት የጀመራቸው ስራዎች አበረታች መሆናቸውን በመግለፅ፣ ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብሏል።

የክትትል ቡድኑ አባላት በቅኝት ሂደት ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ያሏቸውን ነጥቦች በማንሳት ለቢሮው አስተያየት ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘለቃሽ ባህሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር ቢሮ በአገልግሎት አሰጣጡ ለሌሎች ተቋማት ሞዴል ለመሆን አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀው የክትትል ቡድኑ ዳሰሳ በማካሄድ የሰጣቸውን ገንቢ አስተያየቶች በመውሰድ የጀመራቸውን ተግባራት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ይጠቀምባቸዋል ብለዋል።

Additional Images

Additional Image Additional Image Additional Image Additional Image

Share this news

Subscribe to Newsletter

We'll send you notifications when new news is published.

Comments (0)

No comments yet. Be the first to comment!