በሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር
በሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በቢሮው የውስጥ አቅም የበለፀጉ ሲስተሞችን ወደ ስራ ገብተዋል።
ወርቃማ ሰኞ
September 3, 2025
145 views
በሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በቢሮው የውስጥ አቅም የበለፀጉ ሲስተሞችን ወደ ስራ ገብተዋል።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን የሚካሄደው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በቢሮው የውስጥ አቅም በበለፀጉ ሲስተሞች ዙሪያ ገለፃ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።
በገለፃው በsmart customer service እና smart office ዙሪያ በቢሮው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዲ አወል አማካኝነት ገለፃና ማብራሪያ ተደርጓል።
በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ የቢሮው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘለቃሽ ባህሩ ባደረጉት ንግግር ከመጪው ዓለም ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን ዲጂታል ክህሎትን ማዳበር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት በየጊዜው በሚካሄድ ልምምድ ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚደርስ የተናገሩት ኃላፊዋ ከዛሬ ጀምሮ smart office በመጠቀም ስራዎችን ማሳለጥ ይገባል ብለዋል።
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈይሳ ፈለቀ በበኩላቸው በዛሬው ዕለት በውስጥ አቅም ለምተው ወደ ተግባር የገቡ ሲስተሞች አሰራርን ከማቀላጠፍ ባሻገር በውጭ ተቋም ቢለማ ቢሮው ሊያወጣ የሚችለውን ወጪ በማዳን ለተለያዩ ተቋማት ተሞክሮ መሆን መቻሉን አብራርተዋል።
በዛሬው ዕለት ወደ ተግባር የገቡት ሲስተሞች የወረቀት አሰራርን በማስቀረት በቢሮው የሚፃፉ ደብዳቤዎች ዑደት ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ በቢሮው አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ ደንበኞች QR Code በመጠቀም አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
No comments yet. Be the first to comment!