ስለ እኛ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ሥራ ፈላጊዎችን የመመዝገብ ፣ የማደራጀት ፣ ወደ ሥራ የማስገባት ፣ ኢንተርፕራይዞችን የመደገፍ ፣ የገበያ ትስስርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ የማመቻቸት ፣ ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ፍቃድ መስጠትና የመቆጣጠር ፣ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት የሚፈልጉ ዜጎችን የማሰልጠን ፣ የውጭ አገር ሥራ ሰምሪት ኤጀንሲዎችን የመቆጣጠርና ህግና ሥርዓት አክብረው እንዲሰሩ የማድረግ ተግባራትን ያከናውናል። በውስጡም ፦

  • የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ
  • የውጤት ተኮር ትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ
  • የኢንተርፕራይዝ እና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ
  • የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለነዋሪው ህብረተሰብ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ቀልጣፋና በተቀመጠው የአገልግሎት ስታንዳርድ መሰረት በእኩልነት፣ በግልጽነት፣ በፍትሀዊነት እና በወጪ ቁጠባ መርህ መሰረት ለመስጠት እንዲቻል ተቋማት በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በአዲስ መልክ የሥራና ክህሎት ቢሮ በሚል የአደረጃጀትና አሰራር ሪፎርም በማድረግ፤ ብቃትና ተነሳሽነት ያለው፣ ለክህሎት መር ሥራ ፈጠራና ከለውጡ ጋር ራሱን ማስተካከል የሚችል ብቃት ያለው አገልጋይ የሰው ሃይል በመፍጠር ተልዕኳቸውን ይበልጥ ውጤታማ፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመወጣት የሚያስችል እና የተገልጋዩን ፍላጎት ማርካት የሚችል አገልግሎት ለማቅረብ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመተካት ከወረቀት የፀዳ አሰራር ለመፍጠር እንደ ተቋም እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

ተጨማሪ

ተልዕኮ ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ተልዕኮ

ክህሎት መር የውጤት ተኮር የስልጠና ስርዓት በመዘርጋት ብቁ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ የሰው ኃይል ማፍራት

ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ በማድረግ ማልማት እንዲሁም ውጤታማ የሆነ የስራ ስምሪት አገልግሎት በመስጠትና የኢንዱስትሪውን ሰላም ማረጋገጥ

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ኑሮ ማሻሻል

የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን ጤናማ ማድረግ

የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የሚያስችል ተቋም በመገንባት ዘላቂ የስራ እድል እንዲፈጠር ማድረግ

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ምቹ የስራ ሁኔታ የተረጋገጠበት ዘላቂ የስራ ዕድል ተፈጥሮ ማየት፡፡

እሴቶች

የስራ ባሕል ማዳበር

ሙያዊ ልህቀት

ጥራትና ተደራሽነት

አዳዲስ ፈጠራ ማመንጨት

ለለውጥ ዝግጁ መሆን

አካታችነት

ታማኝነት

አገልጋይነት

የቢሮው ጥልቀትና ስፋት

በስሩ የሚገኙ ሰራተኞች ፣ ክፍለ ከተሞች ፣ ወረዳዎችና ኮሌጆች አጠቃላይ መረጃ

ሰራተኞች 227
ክፍለ ከተሞች 11
ወረዳዎች 119
ኮሌጆች 14
የልዕቀት ማዕከል 1
ኢንተርፕራይዞች 3678

አገልግሎቶች

የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና

ለስራ አጥ/ፈላጊዎች የከተማዋ ነዋሪዎች የስራ ስምሪት አገልግሎት መስጠት

ስራና ሰራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት

በኤጄንሲዎች ላይ አቤቱታን መሰረት ያደረገ የቁጥጥር አገልግሎት መስጠት

የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ማቋቋምና ማጠናከር

በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የማድረግ አገልግሎት

የውጤት ተኮር ትምህርት እና ስልጠና

የአሰልጣኞችና አመራሮች ሙያዊ አቅም ግንባታ

የማሰልጠኛ ተቋማትንና ማእከላትን የተደራጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ

በስራ ገበያው ተፈላጊ በሆኑ ሙያዎች (ውጤት ተኮር) የስልጠና አገልግሎት መስጠት

መንግስታዊ ድጋፎች የድጋፍ አገልግሎት መስጠት

የኢንተርፕራይዝ እና ቴክኖሎጂ ልማት

ኢንተርፕራይዞችን ዘርፍ ማህበራትን ማደራጀትና መመዝገብ

ምርታማነትና የማምረት አቅም የመለካት አገልግሎት

የግብኣት፣ የምርት እና የገበያ ትስስር አገልግሎት

የዕድገት ደረጃ ሽግግር አገልግሎት መስጠት

የኢንዱሰትሬ ኤክስቴንሽንና የኢንኩቤሽን አገልግሎት መስጠት

አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን የመቅዳትና የማሸጋገር አገልግሎት መስጠት

የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ

የሥራ ቦታ አከባቢና የሰራተኛች የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ማስጠበቅ

ከስራሁ ኔታዎች ጋር የተያያዘ አቤቱታ መሰረት ያደረገ የህግ ማስፈፀም ቁጥጥር አገልግሎት

የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራት እና የህብረት ስምምነት ምዘገባና እውቅና አገልግሎት የመስጠት

የወል የስራ ክርክሮችን በማስማማት እና በውሳኔ የመፍታት

የባለድርሻ አካላት

መልዕክት

አቶ ጥራቱ በየነ

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ

ክቡራን ተገልጋዮቻችን ማገልገል ክብር ነው! እኛም እናንተን ዝቅ ብለን ስናገለግል ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማናል፡፡ ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎችና ስታንዳርዶች ያለምንም ችግር የማግኘት መብት ያላችሁ ሲሆን የእኛን አገልግሎቶች ለማግኘት ምንም እንቅፋት ቢገጥማችሁ ችግራችሁን ለመፍታትና ችግሩን የፈጠሩ አካላትን በአሰራርና በህግ አግባብ ለመጠየቅ ዝግጁ መሆናችንንና ሁልጊዜም እናንተን ለማገልገል ቢሯችን ሁልግዜም ክፍት መሆኑን ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! አመሰግናለሁ!!

አቶ አስፋው ለገስ ለሙ

በስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ሃላፊ

ወ/ሮ ዘለቃሽ ባህሩ

የስራና ክህሎት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ

ዳግማዊት ግርማ

በስራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ

አቶ መሃመድ ልጋኒ

በስራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ እና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ሃላፊ

አቶ አበበ ተቀባ

በስራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሃላፊ

በስራ አካባቢ ያለው የደህንነት ሁኔታ ክፍተት ያለበት በመሆኑ ክፍተቱን ሊሞላ የሚችል በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለገበያው በማቅረብ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ቢሮው ከኢንዱስትሪዎች ጋር በቅርበት ይሰራል

እኛን ያግኙን

ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለዎት ቢሮአችን በመምጣት ወይም ከታች ባለው መልዕክት ይላኩልን!

አድራሻ

5 ኪሎ ቅድስተ ማርያም, አዲስ አበባ, ኢትዮጲያ

ይደውሉልን

+251 812 45 71

ኢሜል ያድርጉልን

addisabababols@gmail.com

Loading
መልዕክቶዎ ደርሶናል. እናመሰግናለን!